Search

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በጤናው ዘርፍ በአጋርነት መሥራት የሚያስችል የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

ማክሰኞ ታኅሣሥ 14, 2018 414

የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ መንግሥታት በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር የ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የጤና ትብብር ማዕቀፍ ተፈራርመዋል።
የትብብር ስምምነቱ በዘላቂ ልማት፣ በጋራ ኢንቨስትመንትና የጤና ሥርዓትን በማጠናከር ላይ ያተኮረ የኢትዮ-አሜሪካ አዲስ የጤና አጋርነት ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።
የትብብር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ፈርመውታል።
የኢትዮጵያና የአሜሪካ የጤና የአጋርነት ስምምነት ለ5 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፣ የትብብር ማዕቀፉ በኤችአይቪ/ኤድስ፣ ቲቢ፣ ወባ፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና፣ የወረርሽኝ ምላሽ እና ዝግጁነትን የነበረውን ድጋፍ ለማስቀጠል እንዲሁም የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት የበለጠ ለማጠናከር ድጋፍ ለማድረግ ያቀደ ነው።
በኤዶሚያስ ንጉሴ