አሰብ ወደብ ላይ በሩስያ ኤክስፐርቶች እገዛ ኢትዮጵያ የገነባችው የነዳጅ ማጣሪያ አለ። ይህ እአአ በ1964 ተጀምሮ በ1967 የተጠናቀቀው የነዳጅ ማጣሪያ ሥራ ከጀመረ በኋላ ኢትዮጵያ ነዳጅ መግዛት አቁማ ድፍድፉን እያጣራች ትጠቀም ነበር።
ከሻዕቢያ ጋር ይደረግ የነበረው ጦርነት ሲበላሽና የቀድሞው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባላት አሰብን ለቀው መሄዳቸው እርግጥ ሲሆን ታዲያ፣ የተወሰኑ አባላት በከፍተኛ መከፋት እና ተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆነው “የነዳጅ ማጣሪያውን ጠላት እንዳይጠቀምበት ለምን አናወድመውም?” የሚል ሀሳብ ያቀርባሉ።
የቀድሞው ባሕር ኃይል አባላት ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳብራሩት፥ በወቅቱ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ የነበሩት ሪር አድሚራል የኋላሸት ግርማ ግን ይህን ሀሳብ እንደሰሙ፥ “በፍጹም እንዳታደርጉት” ሲሉ የነዳጅ ማጣሪያውን መመታት ተቃወሙ።
አክለውም፥ “Don't do anything. ምንም ነገር እንዳታደርጉ፣ እንዲሁ ትተነው እንሄዳለን፤ አንድ ቀን ተመልሶ የኛ ይሆናል፤ በእኛ ጊዜ ባይሳካ እንኳ፣ የሚቀጥለው ትውልድ ይጠቀምበታል" የሚል መመሪያ በመስጠታቸው በነዳጅ ማጣሪያው ላይ ጉዳት ሳይደርስ መቅረቱን የቀድሞው ባሕር ኃይል አባላት ለኢቲቪ ተናግረዋል።
እናም ለሁሉም ጊዜ አለው እንደሚባለው፣ ጊዜው አሁን ነው፤ ሕጋዊ በሆነ መንግሥታዊ አካሄድ፣ ሰላማዊ በሆነ፣ በሰለጠነ መንገድ በአንድ ወቅት የራሱ የነበረውን የባሕር በር መልሶ ለመውሰድ የሚጠይቅ ትውልድ ተነስቷል።
በዋሲሁን ተስፋዬ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #EthiopianNavy