የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በ4ኛው ዙር የጀጎል ኮሪደር ልማት የተገነባ ከ9 ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ መንገድ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የኮሪደር ልማቱ የጀጎልን ዓለም አቀፍ ቅርስ ከሕልውና አደጋ የታደገ ነው።
ስፍራው ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ደግሞ እጅግ ሳቢ ሆኖ ተገንብቷል ብለዋል።
ቀደም ሲል ለቆሻሻ መጣያነትና ለወንጀለኛ መሸሸጊያነት ያገለግሉ የነበሩ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ በኮሪደር ልማቱ ተቀይረዋል ነው ያሉት።
የልማት ሥራው ከመንግሥት ተጨማሪ በጀት ሳይመደብለት በአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በህዝቡ አንድነት፣ ዳያስፖራውን ጨምሮ በተለያዩ አካላት ከፍተኛ ርብርብ ለስኬት መብቃቱ ተገልጿል።
ለአካባቢ ውበት ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚውም ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተው የጀጎል መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በግንባታው ሂደት ለበርካታ የአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩም ተመላክቷል።
በቴዎድሮስ ታደሰ