Search

ከምቹ መንደር ወደ ምቹ ሀገር

ረቡዕ ጥር 13, 2018 282

በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ ያሉ የመኖሪያ ቤት ልማት ሥራዎች በቤተሰብ ደረጃ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ዘላቂ እና አስተማማኝ መኖሪያዎችን በማስፋት የኑሮ ሁኔታን በማሻሻል ላይ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት አሁንም ከፍተኛ ቢሆንም፥ የኢትዮጵያ መንግሥት መደበኛ የቤት አቅርቦትን ከማህበራዊ ድጋፍ ጋር በማቀናጀት ሰፊ ሥራዎችን እየተከናወኑ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

ቀጣይነት ካላቸው የከተማ እና የህብረተሰብ ተኮር የቤት ልማት መርሐ ግብሮች በተጨማሪ፤ ዓመታዊው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንግሥት ዋነኛ መርሐ ግብር ሆኖ ቀጥሏል።

ይህ መርሐ ግብር በጎ ፈቃደኞችን እና የመንግሥት ተቋማትን በማስተባበር በፈራረሱ ቤቶች ውስጥ ወይም ለጎርፍ አደጋ በሚጋለጡ አካባቢዎች የሚኖሩ አረጋውያንን እና የአቅመ ደካማ ዜጎችን ቤቶች የመጠገንና የመገንባት ሥራ ያከናውናል።

በእነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች አማካኝነት በሺዎች የሚቆጠሩ እና ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑ አባወራዎችና እማወራዎች አስተማማኝ መጠለያ ማግኘት የቻሉ ሲሆን፤ ይህም እንደ ሀገር አካታች ልማትን ለማረጋገጥና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል ኢትዮጵያ እውን እያደረገች ያለውን የማያቋርጥ እድገት ያሳያል ሲል ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።