በብልፅግና ፓርቲ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠልና ለማስፋት በየደረጃው ያሉ አመራሮች በትጋት መሥራት ይኖርባቸዋል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አሳሰቡ፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ሥድስት ወራት የመንግሥትና የፓርቲ አፈጻጸም በአዳማ እየገመገመ ይገኛል።

ከክልል እስከ ቀበሌ በመዋቅር በተሰራው ሥራ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ ተግባር የተከናወነ ቢሆንም፣ ብዙ ቀሪ የቤት ሥራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።
የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት፣ ድህነት፣ ሥርዓት አልበኝነት፣ እና ብልሹ አሰራር በሥራ ታሪክ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።
የተጀመሩ ኢኒሼቲቮች በጥራትና በፍጥነት መሰራታቸውን አመራሩ በትኩረት ሊከታተለው የሚገባው ጉዳይ መሆኑንም አቶ ሽመልስ አስገንዝበዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በሕዝቡ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት በመስጠት ችግሮች እየተፈቱ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ብልፅግና ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ ናቸው።
በፍሬሕይወት ረታ