የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥምረት ለሴቶች ድምፅ ያሰባሰባቸውን አጀንዳዎችን በዛሬው ዕለት ተረክቧል፡፡
ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፣ የሴቶች አጀንዳዎችን ላጠናቀሩት የጥምረቱ አመራሮች በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ የደረሰበት ደረጃና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተም ዋና ኮሚሽነሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በንቃት መሳተፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥምረቱ ድጋፉን ሊቀጥል እንደሚባም በመድረኩ ተነግሯል፡፡
ጥምረቱ ያስረከባቸው አጀንዳዎች በመጀመሪያ ዙር ያልተካተቱትን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ እና አማራ ክልሎችን ያሳተፈ መሆኑን የጥምረቱ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
አሥራ ሦስት አጀንዳዎችና አራት ምክረ ሀሳቦች የተካተቱበት የአጀንዳ ሰነድ የሴቶችን የምክክር ተሳትፎና ውክልና የሚያዳብር እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ አጀንዳዎቹን በቅርቡ ለሚከናወነው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በግብአትነት እንደሚጠቀማቸውም በማሕበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡