የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ12.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በቢሾፍቱ ከተማ እያስገነባው ያለው ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ አቪዬሽንና የቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጋት ነው።
"ትራቭል ኤንድ ቱር ዎርልድ" (Travel and Tour World) በዘገባው እንዳመለከተው፣ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት አየር መንገዱን ከዓከም አቀፍ ግዙፍ ተቋማት ጋር የሚያስተካክለው ነው።
ይህም ይላል "ትራቭል ኤንድ ቱር ዎርልድ" በዘገባው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደነ ሉፍታንዛ፣ ኤር ፍራንስ፣ ኳታር ኤርዌይስ እና ቱርክ አየር መንገድ ካሉ ኩባንያዎች ጋር እኩል ተወዳዳሪ የሚያደርገው መሆኑን በዘገባው አመላክቷል።
አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህ አቅም አየር መንገዱ በአፍሪካ ያለውን የበላይነት ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ለቱሪስቶች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአጠቃላይ አፍሪካን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በእጅጉ ያነቃቃዋል ተብሎም ይጠበቃል።
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የአገልግሎት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣና ለብዙዎች የሥራ ዕድልም ይፈጥራል።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የአፍሪካን እንግዶችና መንገደኞች የማስተናገድ አቅም በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ፣ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ያላትን ስትራቴጂካዊ ተመራጭነት የሚያረጋግጥ "ጨዋታ ቀያሪ" (Game Changer) እንደሚሆን ዘገባው አክሎ ገልጿል።
በላሉ ኢታላ