ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ6 ወራት የሥራ ጉዞ የሚመዝንበትን የግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።

በዚህ የሦስት ቀን መርሐ-ግብር፣ በ2018 በጀት ዓመት አጋማሽ በመንግሥት እና በፓርቲ ሥራዎች የተከናወኑ ዐበይት ተግባራትን፣ ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደር ካለው አመራራችን ጋር በዝርዝር እንደሚገመግሙ ገልጸዋል።
ባለፉት 6 ወራት፣ በ24/7 (ሃያ አራት ሰባት) የተለወጠ የሥራ ባህል፣ ነዋሪዎችን እና የልማት አጋሮችን በማስተባበር በሁሉም ዘርፎች ያቀድናቸውን ሥራዎች በአማካይ 95.3 % ማሳካት ችለናል ነው ያሉት።

ምንም እንኳን የላቀ ውጤት ብናስመዘግብም፣ የታዩ ጉድለቶችን እና የተቋማትን ወጥ ያልሆነ የእቅድ አፈጻጸም፣ በተለይም ፈጣን እና ጥራት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችን፣ አገልግሎት ለመስጠት ጉቦ መጠየቅን፣ የቅንነት መጓደልን በግልጽ በመለየት ለማረም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን የምናስቀምጥበት፤ ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ተጨማሪ አቅምና ተሞክሮ የምንሰንቅበት እንዲሁም የከተማችንን ነዋሪዎች በተሻለ ትጋትና ታማኝነት ለማገልገል የምንዘጋጅበት መድረክ ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል።
ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ለተጉ፣ ለደከሙ መላው አመራሮች እና ሠራተኞችን እንዲሁም እገዛ ላደረጉ የልማት አጋሮች ምስጋና አቅርበዋል።
በኅብር ሠርተን፣ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕያችንን ዳር እናደርሳለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት።
#EBC #EBCdotstream #Ethiopia #AddisAbaba