የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በይፋ መመረቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ በመመረቅ፤ በኢነርጂ ዘርፉ ላይ አዲስ ታሪክ የጻፈ ታላቅ እጥፋት ማስመዝገቧን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ገልጿል።
ይህ ውጤት ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል አማራጮችን ለማስፋፋት የወሰደችው ወሳኝ እርምጃ ምልክት መሆኑም ተገልጿል።
የተረጋጋ የኃይል አቅርቦት በቴክኖሎጂ ለሚመራ ኢኮኖሚ ዋነኛው የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ መጠን፤ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ያላትን ርዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቁርጠኛ ብቻ ሳትሆን ከፍ ያሉ ርዕዮቿን ለመፈፀም በቂ አቅም ያላት መሆኑንም በተግባር እንደሚያሳይም ተመላክቷል።
#EthiopianBroadcastingCorporation #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #PMOEthiopia #Aysha_II #Wind_Power