Search

የሸበሌ ሪዞርት የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ ሥራዎቻችን ማሳያ ነው” - አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ጥር 23, 2018 111

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳቢነት በ"ገበታ ለትውልድ" መርሐ ግብር የተገነባው የሸበሌ ሪዞርት፣ የጎረቤት ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።

በምረቃው ሥነሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ መንግሥት በየአካባቢው ያለውን ሀብት ለመግለጥ የሚያከናውናቸው መሰል ሥራዎች የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ እንደገለጹት፥ በ380 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ሪዞርት፣ 15 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ሰፊ የመልክዓ ምድር ማስዋብ ሥራ ተከናውኖለታል።

ግንባታው የሶማሌ ህዝብን የአኗኗር ዘይቤና ባህላዊ እሴቶች እንዲያንፀባርቅ ተደርጎ የተቀረጸ መሆኑን የገለጹት አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ በሪዞርቱ ከአገልግሎት መስጫ ማዕከላቱ በተጨማሪ 360 ሺህ ችግኞች የተተከሉበት "ፍሩት ፓርክ" መካተቱን አብራርተዋል።

ይህ ፕሮጀክት ከልማት ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የተወጣ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በአካባቢው በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለነበሩ ዜጎች ቁሳቁስ የተሟላላቸው 24 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች ተገንብተው መበርከታቸውን በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም፣ እስካሁን የተገኘውን ተሞክሮ በመቀመር በቀጣይ ለተሻለ ውጤት በትጋት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

#EthiopiaBroadcastingCorporation #TourismEthiopia #LandofOrigins #VisitEthiopia