Search

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬቶች፦ ከማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት እስከ ዕዳ ጫና መቀነስ

ማክሰኞ ጥር 26, 2018 228

የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመራቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች (Economic Reform) ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ይገኛሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በዋናነት ሦስት ግቦችን አንግቦ የተነሳው ይህ ሪፎርም፣ በሁሉም መመዘኛዎች ስኬታማነቱን እያረጋገጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የሪፎርሙ ዋና ዋና ግቦች እና ስኬቶችም፦
የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት፦ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚታዩ አለመረጋጋቶችን በማስተካከል ጤናማ የኢኮኖሚ ሥርዓት መፍጠር።
የኢኮኖሚ ዘርፎችን ማብዛት፦ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅር ከግብርና መርነት ወጥቶ ዘርፈ-ብዙ፣ የብዙ ተዋናዮች ተሳትፎ ያለበት እና ጥራት ያለው ዕድገት እንዲመዘገብ ማድረግ።
የዕዳ ጫናን ማቃለል፦ የኢትዮጵያን የውጭ ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ።
በዚህም ኢትዮጵያ በእነዚህ በሦስቱ ዘርፎች በሁሉም መመዘኛዎች ሊባል በሚችል ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።