በበጀት ዓመቱ 1.2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ያቀደው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 709 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ይህ ውጤት ትልቅ አፈጻጸም ቢሆንም፣ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት አንጻር አሁንም ተጨማሪ ሥራ እንደሚቀረው ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል መንግሥት ካቀደው ጠቅላላ ወጪ ውስጥ በስድስት ወራት ውስጥ ያወጣው 48.5 በመቶ ብቻ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህም በወጪ አጠቃቀም ረገድ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ መከተሉን ያሳያል።
ይህ አፈጻጸም የሀገሪቱን የፋይናንስ አቅም ከማጠናከር ባለፈ፣ የተቀመጡ የልማት ግቦችን ለማሳካት ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።