Search

ከአየር መንገድ ስኬት እስከ ዲጂታል ምጥቀት የኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ በተጨባጭ ቁጥሮች ሲገለጽ

ማክሰኞ ጥር 26, 2018 123

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በምክር ቤት ባደረጉት ማብራሪያ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፖሊሲ ተደግፎ የተከናወነው ሥራ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በቴሌኮም ዘርፍ አስደናቂ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል።
የለውጡ ጅማሬ ወቅት በዓመት 8 ሚሊዮን ደንበኞችን ብቻ ያጓጉዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 10.7 ሚሊዮን መንገደኞችን በማስተናገድ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን በተግባር አረጋግጧል ብለዋል።
በዲጂታይዜሽን ረገድም ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው እድገት እጅግ ፈጣን መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ቀደም ሲል 37 ሚሊዮን የነበረው የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር አሁን ላይ 97 ሚሊዮን መድረሱን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም 58 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ገንዘብ (Mobile Money) ተጠቃሚ መሆናቸው የፋይናንስ ተደራሽነትን ያሳደገ መሆኑን ተናግረዋል።
በቅርቡ ደግሞ የ5ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞች ቁጥር 30 እንደሚደርስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ላይ ገልጸዋል።
ይህ ሁለንተናዊ እድገት በመንግሥት የተቀረጹ ፖሊሲዎች ወደ መሬት ወርደው ውጤት እያመጡ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ተስፋ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተናገሩት።
ኢቢሲ ዶትስትሪም - የመረጃዎ ድልድይ! ሙሉውን ዘገባ እና ዝርዝር መረጃዎችን በኢቢሲ ዶትስትሪም ዲጂታል አማራጮች ይከታተሉ።