Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፡-

ማክሰኞ ጥር 26, 2018 264

👉 ስለ ሀገራዊ ፈተናዎች እና የባንዳነት አመል
• ጠላቶቻችን ኢትዮጵያ ቀና ካለች ሥጋት ስለሚሆንባት "ሳትነሳ እናስቀራት" የሚል ዘመን የማይሽረው ሥጋት አላቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
• በኃይል ችግርን ለመፍታት መሞከር ከጥንት ጀምሮ የተጣባን "በሽታ" ነው ብለዋል፡፡
• ላለፉት 100 ዓመታት ያልተላቀቀን የባንዳነት አመል መኖሩን ጠቅሰው፤ "ባንዳነት ሀገርን ያቆስላል እንጂ አይገልም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
👉 ስለ ሰላም፣ ይቅርታ እና የውይይት በር
• በሀገር ውስጥ የውይይት በርን ክፍት ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ዛሬ ከኢትዮጵያ ተቃርኖ የቆመ ሰው ልብ ገዝቶ በቃኝ ካለ ሁሌም ክፍት መሆን አለብን" ብለዋል።
• በሀገር ጉዳይ ቂም መያያዝ እንደማያስፈልግና "ልቤ ታድሷል" ብሎ ለሚመጣ ማንኛውም አካል በይቅርታ ለማለፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
• በዚህም የተነሳ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ታጣቂዎች ተመልሰው እየገቡ መሆናቸውንና በጫካ ሆነው ከመንግሥት ጋር ትብብር እያደረጉ ያሉት ቁጥራቸው ቀላል እንዳልሆነ ገልጸዋል።
👉 ስለ ትግራይ ሕዝብ ጥበቃ እና የፕሪቶሪያው ስምምነት
• መቐለ ለመግባት አንድ ቀን ብቻ ሲቀረን የፕሪቶሪያውን ስምምነት የፈረምነው ሰላምን በማስቀደም ነው፤ "መቐለ መግባት ድል አይደለም፤ የእኛው ሕዝብ ነው የሚጎዳው" ብለዋል።
• አክሱም ወጣቶች ሲገደሉ፣ ዓድዋ እና ዓዲግራት ሲዘረፍ በርካታ ሰዎችን ወደ ኤርትራ ልከናል፤ የተላኩት ሰዎች ወደ ኤርትራ ያቀኑት የትግራይ ሕዝብ እንዳይነካ ለማድረግ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
• የትግራይ ሕዝብን የሚጠቅም እና የሚጎዳ ነገር የሰራው ይሄ መንግሥት ነው ወይስ አክራሪው ሕወሓት ነው፤ ሕዝቡን የሚጎዳ ነገር የሰራውን አካል ነገ ታሪክ ያወጣዋል ብለዋል፡፡
👉 ብሔራዊ ጥቅም እና የወደፊት ተስፋ
• በብሔራዊ ጥቅም ላይ ያለው ሁኔታ አሁን ላይ በጣም መሻሻሉንና የተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ወደ ሰላም እየመጡ መሆኑን ጠቁመዋል።
• ኢትዮጵያን ያላስቀደመ የፖለቲካ ስብዕና በዘላቂነት በሕዝብ ላይ ጉዳት እንደሚያመጣ ገልጸው፤ የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም በኢኮኖሚ እና በተቋም ግንባታ ማሳደግ የሁላችንም የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።