ኢትዮጵያ ወደ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምታደርገው ጉዞ፣ ከስጋት ወጥተን እንደ በሰለ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለነገው ብሩህ ተስፋ የምንሰለፍበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
ምርጫ ሥልጣን በጋራ ስምምነትና በውክልና የሚገኝበት ዘመናዊ የፖለቲካ መገለጫ ነው።
ምርጫ የሀገር ሕዝባዊ ውል የሚታደስበት፣ የዜጎች ፍላጎትና የሀገር አቅጣጫ የሚናበቡበት የሥልጣኔ መድረክ ነው::
ከዚህም በላይ ደግሞ ሥልጣን ከጠመንጃ አፈሙዝ ሳይሆን በምርጫ ሳጥን የሚረጋገጥ መሆኑ ለሀገራችን የሥልጣኔ ጉዞ ወሳኝ እርምጃ ነው።
ይህ ሂደት ቅቡልነት ያለው መንግሥት እንዲፈጠር፣ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለው መተማመን እንዲጨምር፣ ተጠያቂነት እንዲሰፍንና በኃይል የመገፋፋት ፖለቲካ ቀርቶ የሐሳብ የበላይነት እንዲነግሥ ያደርጋል።
ምርጫን ማካሄድ መቻል የዲሞክራሲያዊ ብስለት ማሳያ ሲሆን፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለፍትሕ ሥርዓቱ መጠናከር የሚያስፈልገውን የተረጋጋ የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠርም ትልቅ መሣሪያ ነው።
#EthiopianBroadcastingCorporation #ኢትዮጵያ #7ኛውጠቅላላምርጫ #ዴሞክራሲ #የነገዋኢትዮጵያ #EBC