Search

ምርጫው አካታች እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

ሰኞ የካቲት 02, 2018 227

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ያካተተና አሳታፊ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶች፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎን ለማሳደግ ያለመ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሯ፤ ምርጫው ነፃ፣ ተዓማኒና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፏቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ በበኩላቸው፤ ምርጫው አካታችና ፍትሐዊ እንዲሆን ቦርዱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፤ የሁሉም ክልሎች የዘርፉ ኃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የተለያዩ አደረጃጀት ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በአባዲ ወይናይ