የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን አጠቃላይ ምርጫ ይፋዊ ውጤት ማሳወቁን ተከትሎ የፈረንሳይ መንግሥት ለምርጫው ስኬታማነት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የፈረንሳይ መንግሥት በመልዕክቱ አዲስ የተመረጡ የፓርላማ አባላትን፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን እንዲሁም በሂደቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና የሲቪክ ማኅበራትን ለስኬቱ አድንቋል፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ ምርጫውን ስኬታማ በሆነ መንገድ ላከናወነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ማስተላለፉን ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።