Search

ኢትዮጵያ ታከናውናለች: የኢትዮጵያ ግብርና 'ኮሜርሻላይዜሽን' ስኬቶች እና የቀጣይ ተስፋዎች

ሓሙስ ሰኔ 18, 2018 49

የሀገራችን የኢኮኖሚ ዋነኛ ምሰሶ የሆነው የግብርና ዘርፍ ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 32 በመቶውን ድርሻ ይይዛል፡፡ 79 በመቶ በላይ ለሚሆነው ሕዝብም ዋነኛ የገቢ እና የመተዳደሪያ ምንጭ ነው።

ባለፉት አምስት ዓመታት ተግባራዊ እየተደረገ ባለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት፣ ዘርፉን ከዕለት ጉርስ ፍላጎት ማሟያነት ወደ ዘመናዊ እና ገበያ ተኮር የንግድ እርሻ (ኮሜርሻላይዜሽን) ለማሸጋገር ታላላቅ የሪፎርም እርምጃዎች ተወስደዋል።

ከእነዚህም መካከል የአነስተኛ አምራቾችን ይዞታ ወደ ከፍተኛ ምርታማነት ሥርዓት ማሸጋገር ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ ቆይቷል።

ለዚህ ስኬት መረጋገጥ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የሚመራው የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮግራም ስትራቴጂካዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት 2011 እስከ 2017 . የተተገበረው የመጀመሪያው የክላስተር ምዕራፍ 4.4 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችን ተደራሽ ማድረግ የቻለ ነው፡፡

በክላስተር የታቀፉ አርሶ አደሮችም ከብሔራዊ አማካዩ 44 በመቶ የላቀ ምርት አስመዝግበዋል።

እንደ ተጨባጭ ማሳያም አማካይ የእህል ምርታማነት መጠን 86 በመቶ በማደግ በሄክታር 3.18 ቶን ደርሷል።

ይህ ከፍተኛ ምርታማነት አጠቃላይ የግብርና ምርትን 56 በመቶ እንዲያድግ አድርጎታል፡፡

አርሶ አደሩ ለራሱ ፍጆታ ከተጠቀመ በኋላ ለገበያ የሚያቀርበው የእህል ትርፍ ምርት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጓል።

ወደ ሆርቲካልቸር ሰብሎች ስንመጣ 2015 . ብቻ ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 658 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ተገኝቷል።

ይህ ገቢ 2005 . ከነበረው 245.6 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር 412.4 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ያሳየ ነው።

በተለይም በአቮካዶ ምርት ላይ የታየው ስትራቴጂያዊ መሻሻል የወጪ ንግድ መጠኑን በማሳደግ 2017 . ወደ 5 ሺህ ቶን እና 1.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ከፍ አድርጎታል።

ለዚህ ዘመናዊ የግብርና ሽግግር የሎጂስቲክስ መሻሻል ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረከተ ሲሆን፣ በአርሶ አደሮች የተመረተውን አቮካዶ በሞጆ ደረቅ ወደብ በማቀዝቀዣ ኮንቴይነር፣ በኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር እና በባሕር ትራንስፖርት ወደ አውሮፓ ገበያ ማቅረብ ተጀምሯል።

የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስም የኢትዮጵያ መንግሥት ከኔዘርላንድስ መንግሥት ጋር በመተባበር 27.5 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚጠይቀውን የማቀዝቀዣ ማዕከል ግንባታን በፍጥነት እያከናወነ ይገኛል።

ይህን ተስፋ ሰጪ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ስኬት ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣ 2017 እስከ 2026 . የሚተገበረው አዲሱ ሀገራዊ የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ሥራ ገብቷል።

ስትራቴጂው በቀጣዮቹ ዓመታት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሙሉ በሙሉ በማሟላት፣ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀዳሚ አምራች እና ላኪ እንዲሁም በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ የማድረግ ታላቅ ራዕይ ሰንቋል።

በዚህም የሆርቲካልቸር ምርቶች ከጠቅላላው የግብርና ዓመታዊ ምርት ያላቸውን ድርሻ 4.5 ወደ 12 በመቶ፣ ዓመታዊ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ወደ 3.3 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም በእሴት ሰንሰለቱ ላይ የሚፈጠረውን ቋሚ የሥራ ዕድል ወደ 2 ሚሊዮን ለማሳደግ ግብ ተቀምጧል።

የተማከለ ዲጂታል የመረጃ ሥርዓት መዘርጋትን ጨምሮ የምርቶችን ደረጃ በመለየት ወደ አውሮፓ እና መካከለኛው ምሥራቅ ገበያዎች የማስፋፋቱ ሥራ የሀገራችንን ተወዳዳሪነት እና የውጭ ምንዛሪ አቅም በእጅጉ የሚያጎለብት ይሆናል።

በለሚ ታደሰ