አላምረው ዋጋው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል የ2018 ትምህርት ዘመን እጩ ተመራቂ ነው፡፡
አላምረው በዩኒቨርሲቲ ቆይታው 4 ነጥብ (CGPA) በማስመዝገብ የዩኒቨርሲቲው ልዩ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ይህ ባለ ብሩህ አእምሮ ወጣት ዕጩ ተመራቂ መሐንዲስ ለዚህ ከፍተኛ ክብር ሊበቃ የቻለው በትምህርት ቆይታው ከወሰዳቸው 55 አጠቃላይ ኮርሶች መካከል በ46ቱን 'A+' እንዲሁም በቀሪዎቹ 9 ኮርሶች 'A' በማምጣት ባስመዘገበው ውጤት ነው።
አላምረው ዋጋው ባሳየው በዚህ አስደናቂ የትምህርት አፈጻጸም፣ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ7ኛው ዙር የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በልዩ ሁኔታ የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን ከአዊ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።