ለዘንድሮው የመኸር እርሻ በቂ የማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት መኖሩን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በ2018/19 የምርት ዘመን 22.9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት አቅዶ 20.9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ መፈፀሙን አስታውቋል።
ከዚህ ውስጥም 13.4 ሚሊዮን ኩንታል ጅቡቲ መድረሱን እና 12.1 ሚሊዮን ኩንታል ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን ተጠቅሷል።
አጠቃላይ የከረመን ጨምሮ 19.1 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለምርት ዘመኑ ለስርጭት የቀረበ ሲሆን እስከአሁን 10.7 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት ተከናውኗል። ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት የ1.4 ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ አሳይቷል።
ያልተሰራጨው ቀሪ ማዳበሪያም ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እና ለማሰራጨት እየተሠራ መሆኑን ተጠቅሷል።
በዚህ ዓመት መንግሥት ለአፈር ማዳበሪያ 84 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉንም የግብር እና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
የምርጥ ዘር አቅርቦቱም በታቀደው መሠረት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለዘንድሮ በቂ የግብአት አቅርቦት መኖሩን እና ከፍተኛ የምርት መጠን እንደሚጠበቅም የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ደሳለኝ ተሻለ ገልጸዋል።
በምርት ዘመኑ የመኸር እርሻ 22 ነጥብ 3 ሚሊየን ሔክታር መሬት በማልማት 730 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስታውቀዋል።
በአባዲ ወይናይ