የካቲት ወር በባርነት እንዲኖሩ የተፈረደባቸው ጥቁር ሕዝቦች ለእኩልነታቸው ያደረጉት ተጋድሎ የሚታሰብበት "የጥቁሮች የታሪክ ወር" (Black History Month) ነው።
ለዘመናት በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል፣ ትናንት በባርነት የታሰሩ እጆች ዛሬ የዓለምን ፖለቲካ ወደሚቀይር የድል መንፈስ እየተሸጋገሩ ይገኛሉ።
የዓድዋ ድል ለአፍሪካውያን እና በመላው ዓለም ለሚገኙ ጥቁር ሕዝቦች "መሸነፍ ዕጣ ፈንታችን አይደለም!" የሚል የሥነ-ልቦና ስንቅ ሆኗቸዋል።
ዓድዋ ላይ የተለኮሰው የድል ችቦ በካሪቢያን እና በሌሎችም አካባቢዎች የነፃነት እና የእኩልነት ራዕይ እንዲሰርፅ ትልቅ መሠረት ጥሏል።
እነ ማርከስ ጋርቬይ ይህን የኢትዮጵያ የነፃነት ብርሃን ተቀብለው አቀጣጥለውታል። በፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ የጋመው ያ የነፃነት ጥያቄ፣ ዛሬ በባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ አማካኝነት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየጻፈ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞትሊ ሀገራቸውን ከብሪታኒያ ንጉሣዊ አገዛዝ አላቅቀው ሪፐብሊክ ከማድረጋቸው ባለፈ፣ ለታሪካዊ በደል የካሣ ጥያቄን በድፍረት በማንሣት የጥቁር ሕዝቦችን ክብር እያስመለሱ ነው።
እኚህ መሪ የኢትዮጵያን የሕዳሴ ግድብ እንደ "ዳግማዊ ዓድዋ" በመጥቀስ፣ ጥቁር ሕዝቦች በራሳቸው አቅም የኢኮኖሚ ነፃነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ እንደሆነ ይናገራሉ።
የጥቁር ሕዝቦች ጉዞ፣ ትናንት በጦር ሜዳ ከተመዘገበ ድል ዛሬ ወደ ዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የተሸጋገረ የጽናት፣ የአንድነት እና የማያቋርጥ የድል ታሪክ ነው።
በዓድዋ የነፃነት ችቦን ለኩሳ በሕዳሴ የደገመችው ኢትዮጵያ በ2030 የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለመሆን እየተጋች ነው።
በ2050 ደግሞ በማክሮ ኢኮኖሚ፣ በዲጂታል ሉዓላዊነት እና በአረንጓዴ ልማት የታጀበ ግዙፍ ኢኮኖሚ በመገንባት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን በጽኑ መሠረት ላይ ታረጋግጣለች።
በለሚ ታደሰ
#Adwa #GERD #africarising #panafricanism #blackhistorymonth #miamottley