ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ታጣቂዎችን የጦር መሳሪያ የመቀበል፣ የማሰልጠን እና ወደ ማኅበረሰቡ የመቀላቀል ተግባር እያከናወነ ነው።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፣ እስካሁን በ4 ክልሎች የነበሩ 90 ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉን ገልጸዋል።
ስልጠናቸውን አጠናቀው ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ የለውጥ ፋና ወጊ እና የሰላም አምባሳደር መሆን እንዳለባቸውም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ኤባ ገርባ፥ የሰላም አማራጭ የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በክልሉ ያለውን ጸጋ በመጠቀም ሕይወታቸውን እንዲቀይሩ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በበኩላቸው “የተሰጠንን ዕድል በመጠቀም ራሳችንን ለመለወጥ እና ማኅበረሰቡን ለመካስ ተዘጋጅተናል” ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም አባገዳዎች ተገኝተዋል።
በአስረሳው ወገሼ