"የማይበገር ፅናት፣ የማይታጠፍ ማንነት!!" በሚል መሪ ቃል የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛው ዓመት የምሥረታ በዓል በሐዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ውጊያን በብቃት የመጨረስ ልዩ ክህሎት ያለውና የጀግናው መከላከያ ሠራዊት ጠንካራ ክንድ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንን ታላቅ በዓል በሲዳማ ክልል ማስተናገድ ታላቅ ክብር መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መከላከያ ሠራዊቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ የሚከፍለውን ወደር የለሽ መስዋዕትነት አድንቀዋል።
አቶ ደስታ አክለውም፣ የሲዳማ ክልል መንግሥት እና ሕዝብ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ለሠራዊቱ የሚያደርጉትን ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ሠራዊቱ ለታላላቅ አገራዊ ተልዕኮዎች ሁልጊዜም ዝግጁ መሆን ስላለበት፣ ሕዝቡ የተለመደ አጋርነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።