Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዘርባጃን ገቡ

ሓሙስ የካቲት 19, 2018 93

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዘርባጃን መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መጥቷል፤ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ ይታያል።

ይኸው ላቅ ያለው የሁለቱ ሀገራት ቅርርብን ተከትሎ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን ነው ጽሕፈት ቤቱ ያስታወቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ ሄዳር አሊዬቭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።

በዚህኛው ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ሲል ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።

#EBC #Ethiopia #Azerbaijan #diplomacy