Search

ከመከፋፈል ወደ አብሮነት፤ የጋራ ትርክት የኢትዮጵያ አዲሱ የመፍትሔ መንገድ

እሑድ የካቲት 29, 2018 142

የጋራ ሀገራዊ ትርክት መገንባት ማህበረሰቡን ለጋራ ዓላማ ለማሰለፍና የዜጎችን የሥነ-ልቦና ውቅር ለመቅረጽ ወሳኝ ስልት ነው።
በቆዩ "ነጠላ ትርክቶች" ምክንያት ማህበረሰቡ በአጥቂ እና በተጠቂ ጎራ ተከፋፍሎ በመቆየቱ በሕዝቦች መካከል የጥርጣሬ ግድግዳ መገንባቱ ብዙ ችግሮች አስከትሏል::
ይህ ዓይነቱ የውስጥ ክፍተት በተለይም በታላቁ የህዳሴ ግድብና በባህር በር ጉዳይ ላይ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎች ለራሳቸው ዓላማ እንደ መግቢያ ቀዳዳ ሊጠቀሙበት ሲፈልጉ ቆይተዋል::
ይህንን ክፍተት ለመሙላት "መደመር" መገለልን አውግዞ፣ አብሮነትን የሚያነግስና በጋራ ትርክት ላይ የተመሰረተ ጉዞ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል።
ትርክት ዝም ብሎ ታሪክ ማውራት ሳይሆን ሕዝብን ለጋራ ግብ የማነቃቂያ ስልት በመሆኑ፣ ለረጅም ጊዜ የዘለቀውንና የጋራ ቤታችንን የናደውን መከፋፈል ማስወገድ ቀዳሚ የቤት ሥራ ነው::
ፖሊሲ የትርክቱ ሥጋ፣ ትርክቱ ደግሞ የፖሊሲው መንፈስ በመሆን ሀገራዊ ተስፋን ለማለምለም ለኢትዮጵያ የመፍትሔ መንገድ እየሆኑ ነው።
በወይንሸት ደጀኔ