Search

የባሕር በር ተፈጥሯዊ መብታችንና የጋራ ሀቃችን ነው፦ ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን

እሑድ የካቲት 29, 2018 159

በአዲስ አበባ ደምቆ በተከናወነው 6ኛው ሀገር አቀፍ የጎዳና ኢፍጣር ላይ የታደሙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የሁላችንም የኢትዮጵያውያን ተፈጥሯዊ መብት መሆኑን ገልጸዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የባሕር በር ጉዳይ የህልውናችንና የብልጽግናችን መሠረት መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ ታሪካዊ መብታችን ያለምንም ውጣ ውረድ፣ በሰላምና በፍቅር እንዲመለስ ያላቸውን ጽኑ ምኞት ለታዳሚው አጋርተዋል።
ይህ የጋራ የባሕር በር ጥያቄ መላው ኢትዮጵያውያንን በአንድነት የሚያቆም ታላቅ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን ያነሱት ሸይኽ አብዱልከሪም፣ ፈጣሪ ለሀገራችን ሰላምን፣ ለሕዝባችን አንድነትን እንዲሁም ለመንግሥታችን ጥንካሬን እንዲሰጥ ተማጽነዋል።
በተለይም ታላቁ የረመዳን ወር በጎ ተግባራት የሚበዙበት ወቅት በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ የጀመረችው የልማትና የሰላም ጉዞ ዘላቂነት እንዲኖረውና የሁላችንም ኩራት የሆነው የባሕር በር ጥያቄ በስኬት እንዲቋጭ ያላቸውን ተስፋ በጸሎት አረጋግጠዋል።
በላሉ ኢታላ