የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ፓርቲውን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመሩና የ2018 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ዘመቻን የሚያስተባብሩ መሪዎችን መርጧል።
በዚህም መሠረት ለፓርቲው መሪነት የቀረቡትን ዕጩዎች በማወዳደር አቶ ኢዮብ መሳፍንት በድምፅ ብልጫ የኢዜማ መሪ በመሆን ኃላፊነቱን ተረክበዋል።
በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ተመራጭ መሪዎች ለአንድ የመንግሥት የሥልጣን ዘመን ማለትም ለአምስት ዓመታት የሚያገለግሉ ይሆናል።
ከመሪዎች ምርጫ ጎን ለጎንም ጉባኤው ለ2018 ምርጫ ያዘጋጀውን የኢዜማ "ነጩ የቃል ኪዳን ሰነድ" ጨምሮ፣ ያሻሻላቸውንና እንደ አዲስ የጨመራቸውን ፖሊሲዎች በአንድ ድምፅ አፅድቋል።
በአሥር ምዕራፎች የተከፋፈለው ይህ የቃል ኪዳን ሰነድ፣ ቀደም ሲል የነበሩትን 42 የፖሊሲ አማራጮች በማሻሻልና ስምንት አዳዲስ ፖሊሲዎችን በማካተት በአጠቃላይ 50 የፖሊሲ አማራጮችን የያዘ መሆኑ ታውቋል።
ይህም ፓርቲው ለቀጣዩ ምርጫ ያለውን ዝግጁነት የሚያሳይ ታላቅ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
ብሩክታዊት ተገኝ