Search

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ሓሙስ ሚያዝያ 15, 2018 159

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 50.5 ሚሊዮን መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ እስከ ትናንት ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሲከናወን የነበረው የመራጮች ምዝገባ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ከሰብሳቢዋ መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በአጠቃላይ ከተመዘገቡት መራጮች መካከል 5.5 ሚሊዮን የሚሆኑት "በምርጫዬ" የሞባይል መተግበሪያ (App) አማካኝነት የተመዘገቡ ናቸው።

ይህ አኃዝ የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓቱ ለዜጎች ምቾትን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ያሳያል ተብሏል።

ቦርዱ የምዝገባ ሂደቱ በሰላም መጠናቀቁን ገልጾ፣ ለሂደቱ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ አካላትና ለመራጮች ምስጋና አቅርቧል።

በለሚ ታደሰ

#Ethiopia #EBC #EthiopianElection #NEBE #VoterRegistration #MirechayeApp