Search

በድሬዳዋ ከተማ ያየናቸው የኮሪደር ልማት ሥራዎች እጅግ አስደማሚ ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ የካቲት 30, 2018 66

በድሬዳዋ ከተማ የተመለከትናቸው የኮሪደር እና የልማት ሥራዎች እጅግ አስደማሚ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በበረሃዋ ንግሥት” ድሬዳዋ ባደረጉት ጉብኝት በደቻቱ፣ ኮኔል፣ ቀፊራ፣ ለጋሃሬ እና ከዚራ የታየው ለውጥ ከአምናው በብዙ እንደሚለይ እና የተሠራው ሥራ የሚታይ ለውጥ መሆኑን አንሥተዋል።

አብዛኞቹ የከተማዋ ክፍሎች በኮሪደር ልማቱ እጅግ እየተዋቡ መምጣታቸውን ያነሡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በድሬዳዋ የተገነቡ መንገዶች የሥራው አንድ አካል መሆናቸውን እና አሁንም ሰፊ ሥራዎችን መሥራት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

“በከተማዋ ያሉ ሕንፃዎች ቢሮ ብቻ መሆን የለባቸውም፤ ወደ ገቢ ምንጭነት ተቀይረው የከተማውን ልማት ማገዝ አለባቸው። ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ተጨማሪ የቤት ሥራ ወስዶ መሥራት ይኖርበታል” ነው ያሉት።

በድሬዳዋ ከተማ እየታየ ያለው የልማት እንቅስቃሴ እያደገ ቢሆንም፣ በሆቴል እና ሬስቶራንት ዘርፍ ላይ ያለውን ክፍተት መሙላት እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#EBC #Ethiopia #PMAbiy #DireDawa