Search

ኢትዮጵያ ገና ያልተነኩና ያልታወቁ በርካታ ሀብቶች አሏት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ መጋቢት 01, 2018 32

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ የሚገኘውን ታሪካዊውን የናሲኦል ዋሻ በጎበኙበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ ገና ያልተነኩና ያልታወቁ በርካታ ሀብቶች እንዳሏት ገልፀዋል።

በአካባቢው ያለው የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሀብት ተሰናስሎ መዝለቅ እንዳለበት የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እንደ ሸበሌ ፍልውሃ ያሉ የቱሪዝም እና የልማት ጸጋዎችን በማልማት ጅግጅጋን፣ ሐረርንና ምሥራቅ ሐረርጌን በኢኮኖሚ ማስተሳሰር እንደሚቻል አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ገና ያልተነኩና ያልታወቁ በርካታ ሀብቶች እንዳሏት የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የኢትዮጵያ የልማት ስትራቴጂዎች በባዕዳን መረጃ ላይ መደገፍ የለባቸውም ብለዋል።

ኢትዮጵያ በራሷ መረጃና ሀብት ላይ የተመሠረተ የልማት ፖሊሲ መቅረጽ እንዳለባት ጠቅሰው፤ የሀገራችንን እውነተኛ ገጽታ ለማሳየት "የዳታ ሉዓላዊነት" ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

አንድ ሀገር በራሱ ሉዓላዊ በሆነ መረጃ ላይ ተንተርሶ የሚቀርጸው ፖሊሲ እውነተኛና የሀገሪቱን መልክና ቅርጽ በትክክል የሚያሳይ መሆኑን ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከሌሎች በሚገኝ መረጃ ላይ ተንተርሰው የሚሰሩ ፖሊሲዎች የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ስለማይወክሉ የተሟላ ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያን ዕድገት ለማፋጠን በራስ መረጃና ሀብት ላይ የተመሠረተ የልማት አቅጣጫ መከተል አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#EBC #Ethiopia #AbiyAhmed #NasiolCave #EastHararghe #DataSovereignty #RegionalIntegration