Search

በጋሞ ዞን ደጋማ ቀበሌዎች የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት የ30 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ረቡዕ መጋቢት 02, 2018 205

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ደጋማ ቀበሌዎች የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። 

አደጋው የተከሰተው ከሰሞኑን በተከታታይነት እየጣለ ያለውን ዝናብ ተከትሎ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ከመላክቷል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

በተያያዘም በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ስጋት መጋረጡ ተገልጿል። 

በተለይም በአርባ ምንጭ ዙሪያ፦ ወረዳ ቆላ ሼሌ፣ ሼሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌያት፤ በከምባ ዙሪያ ወረዳ፦ ባልታ ቀበሌ እና አካባቢው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰትባቸው የሚችሉ ቀጠናዎች መሆናቸው ተነግሯል።

በመሆኑም በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የከፋ አደጋ እንዳይደርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ተጋላጭ ከሆኑ ስፍራዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ መልዕክት ተላልፏል።

በተመስገን ተስፋዬ 

#Ethiopia #Gammo #rain #flood