Search

በሐረሪ ክልል በሀገራዊ ለውጡ ለተገኘው ስኬት እውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ሰኞ መጋቢት 28, 2018 401

ሀገራዊ ለውጡ እውን መሆን የጀመረበትን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለተገኘው ስኬት እውቅና የሚሰጥ በሐረሪ ክልል የሚገኙ የከተማና የገጠር ወረዳዎች ነዋሪዎች የተሳተፉበት የድጋፍ ሰልፍ በኢማም አህመድ ስታዲየም እየተካሄደ ነው።
በስታዲየሙ የተገኙ ተሳታፊዎች የለውጡን ጉዞ የሚደግፉና ለቀጣይ ስኬቶች ያላቸውን ዝግጁነት የሚገልጹ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ከተደመጡት መፈክሮች መካከልም "ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልፅግና!"፣ "እሳቢያችን ዘመን ተሻጋሪ፣ ተግባራችን ትውልድ ቀያሪ!"፣"ሐረርን ከቀደምት ከተማነት ወደ ብልፅግና ተምሳሌትነት እናሸጋግራለን!" የሚሉ ይገኙበታል።
ሰልፈኞቹ መጋቢት 24 በኢትዮጵያ እውነተኛ የዲሞክራሲ ግንባታ የተረጋገጠበትና ሀገሪቱን የማላቅ ጉዞ የተጀመረበት ቀን መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም በመስዋዕትነት የተገኘውን ድል በተባበረ ክንድ ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት አስተጋብተዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ