ጋሽ በለጠ ባሹ ይባላሉ፡፡ ዳውሮን ከጅማ የሚያገናኝ መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስገነቡ የመንደር አድባር ናቸው።
ጋሽ በለጠ ባሹ በታርጫ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የአካባቢው አድባር፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚከበሩ የተጣላን የሚሸመግሉ አስታራቂ እንደሆኑም ይወሳል።
በአካባቢያቸው ነዋሪዎች ዘንድ እስከዛሬም ከሚያስመሰግኗቸው ጉዳዮች አንዱ፤ የአውራጃ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ዳውሮን ከጅማ የሚያገናኝ መንገድ ማሰራታቸው እንደሆነ ያነሳሉ።
ጋሽ በለጠ ባሹ፤ "ሰው ሲጣላ ማየት አልወድም፤ ከልጅነቴ ጀምሮ የተጣሉትን ማስታረቅ እወዳለሁ" ይላሉ።
የመንደር አድባር የሆኑት ጋሽ በለጠ፤ ሰው ሲጣላ አጥፊውን ተቆጥቼ ተበዳዩንም ለምኜ አስማማለሁ ሲሉም ከቅዳሜ አመሻሽ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
በአንድ ወቅት በነበረ ግጭት ወጣቶች ተደራጅተው ተቋም ሊያቃጥሉ ሲሉ መክረው እና ገስፀው ማስጣላቸውን ያስታውሳሉ።
በአካባቢው ማኅበረሰብ የሚመሰገኑት ጋሽ በለጠ ባሹ፤ አርዓያ የሚሆኑ የተከበሩ የታርጫ ከተማ የመንደር አድባር ናቸው።
በሔለን ተስፋዬ
#ebc #ebcdotstream #kidameameshash #ቅዳሜ_አመሻሽ