የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ግጭት ወደ ማብቂያው ምዕራፍ እየተቃረበ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት በሩሲያና በመላው ዓለም የተከበረውን የድል ቀን በዓል ተከትሎ በሞስኮ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።
ፕሬዚዳንት ፑቲን በሰጡት ማብራሪያ "ጉዳዩ ወደ ዩክሬን ግጭት ማጠቃለያ እያመራ ነው ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም በሩሲያና በዩክሬን መካከል የመጨረሻው የሰላም ስምምነት ላይ መድረስ ከተቻለ፣ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በሦስተኛ ሀገር ለመገናኘትና ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በሞስኮ በተካሄደው የድል ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ከመጡ የውጭ ሀገራት መሪዎች ጋር ተከታታይ ስብሰባዎችን ያደረጉት ፑቲን፣ ስለ ሩሲያ-ቻይና ግንኙነትና ስለ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችም ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ግጭቱን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ ስምምነቶች ላይ መድረስ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውበታል።
በብሌን ደምበሎ