Search

በምርጫ ካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል፦ የምዕራብ አርሲ ዞን አርሶ አደሮች

ዓርብ ግንቦት 21, 2018 60

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ብቻ መቅረታቸውን ተከትሎ፣ የምዕራብ አርሲ ዞን አርሶ አደሮች በሂደቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡

የምርጫ ካርድ የወሰዱት የዞኑ ነዋሪዎች እንደሚሉት የሀገር እና የሕዝብ ጥቅም እንዲከበር ጠንካራ መንግሥት ያስፈልጋል፡፡

ይህ ደግሞ ዕውን እንዲሆን የዜጎች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የአንዲት የምርጫ ካርድ ድምፅ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አሸናፊነት ከመወሰን ባለፈ፣ የሀገርን መጻኢ ዕድል በመወሰን ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳላትም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ዜጎች ነገ የሚፈልጉትን አስተዳደር ዛሬ በራሳቸው ፈቃድ ውሳኔ የሚያሳርፉበት እና ማረጋገጫ የሚሰጡበት ሂደት በመሆኑ፣ ሁሉም ማኅበረሰብ በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

በአስረሳው ወገሼ