የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶችን በይፋ እየተቀበለ መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አስታውቀዋል።
ሰብሳቢዋ እንደገለጹት፣ የቦርዱ ሠራተኞች ሂደቱን በስኬት ለማጠናቀቅ የማጣራት ሥራዎችን ቀንና ሌሊት በከፍተኛ ትጋትና በቅንጅት እያከናወኑ ይገኛሉ።
እስካሁን ባለው ሂደት 497 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውጤት ወደ ማዕከል መድረሱን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።
በተጨማሪም 634 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ውጤት ወደ ማዕከል መድረሳቸውን ጠቅሰዋል።
በአጠቃላይ 1 ሺህ 131 የምርጫ ውጤቶች ወደ ማዕከል መድረሳቸውንም አረጋግጠዋል።
በተያያዘም ቅሬታ የቀረበባቸው የምርጫ ክልል ውጤቶች በጥንቃቄ እየታዩ መሆኑን ተናግረዋል።
የክርክሩ ሂደት ሕጋዊ ፍጻሜ እስኪያገኝ ድረስ የእነዚህ አካባቢዎች ውጤት ይፋ እንደማይደረግ ገልጸዋል።
በማጣራት ሂደቱ የምስክሮች በትክክል አለመቅረብ በሥራው ላይ መጠነኛ መዘግየት እየፈጠረ እንደሚገኝም ተናግረዋል።