Search

ዜጎችን ከጤና እክል እና ከአደጋ የጠበቀው የወንዝ ዳርቻ ልማት

Aug 12, 2025

በአዲስ አበባ እየተከወነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ለጤና ስጋት የነበሩ አከባቢዎችን ወደ መዝናኛ እና ምቹ ቦታነት እየቀየራቸው ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም ለበርካታ ነዋሪዎች ንብረት እና ሕይወት መጥፋት ምክንያት የነበሩ ስፍራዎች አሁን ላይ አረንጓዴ ልማት ተከናውኖባቸዋል።

በአዲስ አበባ ከቀበና ድልድይ እስከ እንጦጦ ተራራ ያለው የወንዞች ዳርቻ ልማት ለዚህ በጎ ተግባር በአብነት ተጠቃሽ ከሆኑት መካከል ዋነኛው ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጥላሁን ወርቁ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ የአዲስ አበባ ወንዞች ከዚህ በፊት በወንዙ ዙሪያ ለሚኖሩ ዜጎች የአደጋ ስጋት ነበሩ፣ በተጨባጭም አደጋ ሲያስከትሉ ቆይተዋል።

ወንዞች የደረቅ እና የፍሳሽ ቆሻሻ መጣያ ሆነው እንደነበር አስታውሰው ፤ለብዙ ዜጎችም የጤና ጠንቅ ሆነው እንደበረም ነው ያስረዱት፡፡

ወንዞች የደረቅ እና የፍሳሽ ቆሻሻ መጣያ ሆነው እንደነበር አስታውሰው ፤ለብዙ ዜጎችም የጤና ጠንቅ ሆነው እንደበረም ነው ያስረዱት፡፡

"በከተማዋ በስፋት እየተሰራበት የሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት ከልማት ባሻገር ላቅ ያለ ዓላማን ያነገበ ነው" ብለዋል፡፡

የልማት ሥራው የዜጎችን ሕይወት የማሻሻል አካል መሆኑን ጠቁመው፤ ከተማዋ እጅጉ እያደገች እና ለነዋሪዎቿ ምቹ እየሆነች እንዳለም ነው የገለጹት፡፡

አሁን ላይ ግን ወንዞችን ንጹህ ከማድረግ ባሻገር ለነዋሪዎች ምቹ እና ውብ መናፈሻዎች መገንባታቸውን አንስተዋል፡፡

ይህ የወንዝ ዳርቻ ልማት "የይቻላል ሀሳብን የገነባ” ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ልማቱ ለወጣቱ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር፤ የወንዝ ዳርቻ ልማቱን ተከትሎ የንግድ ቦታዎችን መስፋፋታቸውንም ነው የገለጹት፡፡

ወንዞችን የሚያገናኙ በርካታ ድልድዮችም መገንባታቸው አቶ ጥላሁን ወርቁ  አስታውቀዋል።

 

በሜሮን ንብረት