የኢጋድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ያካሄደችውን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ አድንቀዋል።
ከዚህ ቀደም በርካታ ምርጫዎችን እንደታዘቡ የገለጹት ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የታዘቡት ምርጫ ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ የታየበት በአካታችነቱም የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ በይበልጥ የተመለከቱበት እና ከሌሊት ጀምሮ ረጃጅም ሰልፎች እንዳስተዋሉ ገልጸዋል።
የቡድኑን መሪዋ ሕዝቡ ድምፁን ለመስጠት የተሰለፈው “እጅግ ረጅም” ሲሉ የገለጹት ሰልፍ አጋጥሟቸው እንደማያውቅ በአድናቆት ገልጸዋል።
“የኢትዮጵያ ሕዝብ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ሲመርጥ ነበር፤ ይህም ሕዝቡ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሰጠውን ትኩረት የታዘብንበት ምርጫ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል።
የአፍሪክ ኅብረት እና የኢጋድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት ዙሪያ ያቀናጁትን የመጀመሪያው የግምገማ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ