Search

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያና የምርጥ ዘር ሥርጭት አየተከናወነ ነው

እሑድ ሰኔ 14, 2018 74

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 2018/19 የመኸር እርሻ ለአርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያና የምርጥ ዘር ሥርጭት አየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።

በቢሮው የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ ተሰፋዬ በቀለ እንደገለጹት፣ እስካሁን 98 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ ገብቶ ለአርሶ አደሮች የማሰራጨት ስራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በክልሉ በተያዘው 2018/19 የመኸር ምርት ዘመን 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በተለያዩ አዝዕርቶች በመሸፈን 70 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

የአሶሳ ዞን አርሶ አደሮች የሆኑት አልማሃዲ አህመድ እና ፈይሰል ኑሬ በምርት ዘመኑ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ከማሳ ዝግጅት ጀምረው የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

 

 

በዚህም አሁን ላይ የክልሉ ግብርና ቢሮ ያቀረበላቸውን የምርጥ ዘርና አፈር ማዳበሪያ ግብዓት መረከባቸውን አንስተው፣ በተያዘው የምርት ዘመን የተሻለ ምርት ለማግኘት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተግተው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጀማል አህመድ