Search

ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመራበት መንገድ ሚደነቅ ነው - የአፍሪክ ኅብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን

ረቡዕ ግንቦት 26, 2018 114

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመምራት ያደረገው ዝግጅት እና ምርጫውን ያስፈፀመበት አቅም የሚደነቅ መሆኑን የአፍሪክ ኅብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን መሪዎች ገለጹ።

የአፍሪክ ኅብረት እና የኢጋድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን አጠቃላይ የምርጫው ሂደት ዙሪያ ያጠናቀሩትን የመጀመሪያው የግምገማ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

በመግለጫቸውም ምርጫ ቦርድ ያሳየው ገለልተኝነት፣ የቴክኖሎጂ ዝግጅቱ፣ አካታችነቱ እና የምርጫው አስተዳደር ጠንካራ ነበር ብለዋል።

እጩ ተመራጮች እና መራጮች በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴክኖሎጂ የታገዘ ምዝገባ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል።