የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ (አፕ) በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል።
የዲጂታል ኢቢሲ ምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አትሌቶች፣ አርቲስቶች፣ የተቋሙ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢቢሲ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን እና በዶትስትሪም የማኅበርራዊ ሚዲያ አማራጮቹ የሚሠራቸውን ይዘቶች በአንድ ቦታ በሞባይል መተገበሪያው ማግኘትን የሚያስችል ነው።
የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ አካል የሆነው ዲጂታል ኢቢሲ ሁሉንም የይዘት አማራጮቹን በቀላሉ እና በአንድ ቦታ ማግኘት የሚያስችል ሆኗል።
ዲጂታል ኢቢሲ እውን የሆነበት የሞባይል መተግበሪያ ሁሉንም አይነት ዜናዎች፣ የድምጽ እና የምስል መረጃዎችን በፍጥነት ማግኘት ያስችላል።
የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ የቀጥታ ስርጭቶች ሳይቆራረጡ በተፈለገው ቦታ ሁሉ ለማግኘት ትክክለኛው ምርጫ የኢቢሲ ሞባይል መተግበሪያ ነው።
አሁን ላይ መረጃዎች በዲጂታሉ ዓለም ውስጥ በእጅ ስልክ እየደረሱ ባለበት ወቅት የኢቢሲን ይዘቶች በቀላሉ ለማግኘት የሞባይል መተግበሪያ ትክክለኛ ምርጫ ይሆናል።
የሞባይል መተግበሪያውን ለአንድሮይድ (Android) ስልክ https://shorturl.at/6KegY እንዲሁም አይኦኤስ (iOS) ስልክ ደግሞ https://shorturl.at/hFuA1 ገብተው በማውረድ ዲጂታል ኢቢሲ ይቀላቀሉ።
በተጨማሪም የኢቢሲ ድረ ገፅን www.ebc.et ገብተው ያሉ የመረጃ ሃብቶችን ገብተው እንዲመለከቱ እንጋብዛለን።
የ25 60 90 ዓመታት የሬዲዮ፣ የቴሌቪዥን እና የኤፍ ኤም የይዘት ሃብቶች ከዶትስትሪም የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች ጋር በአንድ ቦታ ለማግኘት የእጅ ስልክዎ ከምንጊዜው በላይ ወደእርስዎ ቀርቧል።