Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

ዓርብ ግንቦት 28, 2018 258

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት የኀዘን መግለጫ፣ “በቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር አሊ አብዶ ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል።” ብለዋል።

አምባሳደር ዓሊ አብዶ 27ኛ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በመሆን እንዲሁም በሱዳን እና በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሀገራቸውን ያገለገሉ የሀገር ባለውለታ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለመላው ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተው፣

“ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር” ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: