Search

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በንቃት የተሳተፉበት ምርጫ ነው - የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማኅበር

እሑድ ግንቦት 30, 2018 53

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በንቃት የተሳተፉበት ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት እናታለም እንዳለ ገለጹ።

ምርጫውን ከታዘቡት 55 የሀገር ውስጥ ሲቪክ ማኅበራት መካከል አንዱ የሆነው የማኅበሩ ፕሬዚዳንት እናታለም እንዳለ እንደገለጹት፣ ምርጫ ዜጎች መብታቸውን ተጠቅመው የሚበጃቸውን ፓርቲ የሚመርጡበት የዴሞክራሲ መገለጫ ነው።

ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሁሉም ማኅበረሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ የተረጋገጠበት የፖለቲካ ዓውድ ነበር ብለዋል።

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፈቃድ በመውሰድ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በጠቅላላ ምርጫው ንቁ ተሳታፊ የሚሆኑበትን የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርት መስጠታቸውን ገልጸዋል።

ከሁለት ሺህ በላይ አባላትን በማሠልጠን በዕለቱ የምርጫ ታዛቢዎችን መመደባቸውን እና በርካታ ዜጎች የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ድምፅ መስጠታቸውንም ተናግረል።

ዜጎች ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ድምፅ መስጠታቸውን በማንሣት፣ የሕዝቡን ተነሳሽነት እና ፍላጎትም ማድነቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማኅበር 1990 . የተቋቋመ፤ አሁን ላይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ አባላት አሉት።