Search

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ብራሰልስ በረራ የጀመረበትን 20ኛ ዓመት አከበረ

ዓርብ ግንቦት 28, 2018 50

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቤልጂየም ርዕሰ መዲና እና የዓለም ዲፕሎማሲ መዲና ወደሆነችው ብራሰልስ በረራ የጀመረበትን 20 ዓመት በደማቅ ሥነ ሥርዓት አክብሯል።

አየር መንገዱ፣ "ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ወደ ብራሰልስ ባደረግናቸው ጉዞዎች አብራችሁን ለነበራችሁ ውድ መንገደኞቻችን እና አጋሮቻችን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን" በማለት በማኅበራዊ ገጹ መልዕክቱን አስተላለፏል።

አየር መንገዱ በቀጣይም የላቀ መስተንግዶውን ይዞ ደንበኞቹን ይዞ ይበልጥ በብቃት ለማገልገል ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።