Search

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው አዲስ የዲኤንኤ (DNA)፣ የፎሬንሲክ እና ሥነ-ምረዛ ምርመራ የልህቀት ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ

ዓርብ ግንቦት 28, 2018 51

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ፣ የሕዝቡን የጤና አገልግሎት በአዲስ ከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ አዲስ የዲኤንኤ (DNA) የፎሬንሲክ እና ሥነምረዛ ምርመራ የልህቀት ማዕከልን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ሀገራችን ብዙ የውጭ ምንዛሪ የምታጣበት እና የምርመራ ውጤት ለማግኘት በጣም

ሆስፒታሎች በመገንባት እና ነባሮቹንም ሆስፒታሎች በማደስ እና በማስፋፋት ሰፊ ሥራዎችን ሠርተን አዘምነናቸዋል ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

በከተማ አስተዳራችን በጤናው ዘርፍ የኢትዮጵያን የዕድገት ተምረጅም ጊዜ ይፈጅ የነበረውን ችግር የሚያስቀር DNA መረጃ ማከማቻ እና ማነጻጸሪያ ሲስተም (CODIS) በወንጀል የተጠረጠሩ፣ ወላጅነትን ለማረጋገጥ እና ተመሳሳይ ምርመራዎችን በዘር መለያ (DNA Profiling) ለመለየት፣ የቤተሰብ ግንኙነትን እስከ ዘር ሐረግ መለየት እና ማረጋገጥ እንዲሁም አጠራጣሪ ማንነትን ለማወቅ የሚያስችል የልህቀት ማዕከል ነው ብለዋል።

ይህ ማዕከል የሀገራችንን የፍትሕ ሥርዓት ምርመራን ውጤታማ በማድረግ እና በማዘመን፣ በሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ የወንጀል ምርመራ ለማካሄድ፣ የመብት ጥያቄዎችን ለመመለስ እና ለሕዝብ ጤና ጥበቃ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ብሔራዊ የልህቀት ማዕከል እንደሆነም ጠቁመዋል።

ሁሌም ቃልን በተግባር ፈፅመን በቁርጠኝነት እና በተሻሻለ የሥራ ባህል እየሠራን ባለፉት 5 ዓመታት ለጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት 4 ዓለም አቀፍ ደረጃ የሚመጥኑ ሳሌትነት እና የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ምዕራፍ እያበሰርን ነው! ተጠናክሮም ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን የጤና ባለሙያዎችን ትጋት፣ ብቃት እና እምነት ይበልጥ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ከዕቅድ ጀምሮ የልህቀት ማዕከሉ እውን እንዲሆን አስተዋዕኦ ያደረጉትን በሙሉ በራሳቸው፣ በከተማ አስተዳደሩ እና በተጠቃሚዎች ስም ከልብ አመስግነዋል።