Search

የኢቢሲ ዲጂታል አሠራር እና የይዘት ስብጥር ለሚዲያዎች አዲሱን ምዕራፍ የከፈተ ነው:- ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

ረቡዕ ነሐሴ 07, 2017 136

የኢቢሲ ዲጂታል አሠራር እና የይዘት ስብጥር የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ እና ለሌሎችም ሚዲያዎች አዲሱን ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እና የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ።
መረጃ የሰዎችን የዕለት ከዕለት ኑሮ በብዙ መልኩ በሚዳስስበት በዚህ ጊዜ፣ ኢቢሲ መረጃን በተለያዩ አማራጮች የሁሉንም መልክ በሚያሳይ መልኩ ተደራሽ ማድረጉ ለኢትዮጵያ ሚዲያ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑንም አንሥተዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ መረጃ በሰከንዶች ልዩነት ዓለምን በሚያካልልበት በዚህ ጊዜ የተዛቡ ትርከቶችን የሚያስተላልፉ በርካቶች እንዳሉም ሚኒስትሩ አንሥተዋል።
ይህን መቀልበስ የሚችል፣ የሀገርን መልክ የሚገነባ፣ ዜጎችን የሚያቀራርብ እና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብሩ ይዘቶችን ኢቢሲ በዲጂታሉ ዓለም የሚያደርስ አሠራርን ማጎልበቱ ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሚዲያዎች የሐሰት ትርክትን በመመከት፣ የሀገራችንን የዕድገት አውዶች በማሳየት ብሎም ኢትዮጵያዊ ጣዕም ያላቸውን ይዘቶች በማምረት ላይ መሥራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
ለዚህም ኢቢሲ ከ10 በላይ የይዘት ምንጮችን ከ25 በላይ ዲጂታላይዝድ ሲስተሞችን ተጠቅሞ ተደራሽ ለማድረግ የጀመረው ጉዞ ትልቅ ማሳያ ነውም ብለዋል ሚኒስትሩ።
ኢቢሲ ወደ ዲጂታል ምዕራፍ ሲሸጋገር አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሁሉም ባለድርሻዎች ምስጋና ይገባልም ነው ያሉት።
በሰለሞን ከበደ