Search

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የኢቦላ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችል የባለሙያች የተግባር ልምምድ ተመለከቱ

እሑድ ግንቦት 30, 2018 51

የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ዝግጁነት ለማጠናከር ይቻል ዘንድ በኅብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር የመግቢያ እና መውጫ የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የጤና ልየታ፣ የቁጥጥር እና የቅኝት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የባለሙያዎች ተግባራዊ ልምምድ (Simulation exercise) እየተደረገ ይገኛል።

ልምምዱን የተመለከቱት የጤና ሚኒስትር / መቅደስ ዳባ፣ ኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በዩጋንዳ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከልን በማጠናከር ጥብቅ የሆነ የቅኝት እና የልየታ ሥራ እንዲሠራ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ወረርሽኞችን ከመከላከል እና ከመቆጣጣር አንጻር ከዚህ በፊት የነበሩትን ልምዶች እና አሁን የተገኘውን እውቀት መሠረት በማድረግ በቀጣይ እስከ ታችኛው የጤና ተቋም እና የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ባለሙያዎች በማውረድ ሁሉም ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራችንን፣ ቤተሰባችንን፣ ኅብረተሰባችንን ከማንኛውም የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ችግሮች በመጠበቅ እና በመታደግ ለትውልድ የሚሻገር ሥራ በመሥራት ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉም ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።