የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት የሚካሄደውን አራተኛውን የአማራ ክልል "ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ-ግብርን አስጀምረዋል።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ከርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ መሪዎች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በክልሉ "ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ ልምድ የሚለዋወጡበት እና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ኤክስፖ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በኤክስፖው 145 አምራች ኢንዱስትሪዎች እየተሳተፉ ነው።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር አድርጓል። እንደማነቆ የሚያነሷቸው ችግሮችም እንዲፈቱ እያደረገ ነው።