Search

የኢቢሲ የዲጂታል መተግበሪያ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ አካል ነው - አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ

ረቡዕ ነሐሴ 07, 2017 156

የኢቢሲ የዲጂታል መተግበሪያ ወደ ስራ መግባት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ አካል መሆኑን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለፁ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ (አፕ) በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በሰጡት አስተያየት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ኢቢሲ በራሱ አቅም ልዩ ዲጂታል መተግበሪያን ማበልፀጉ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

ተቋማት የአሁኑ እና የቀጣዩ ዘመን እውነታ የሆነውን ዲጂታላይዜሽንን በራሳቸው አውድ እውን ማድረግ እንደሚገባቸውም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

ዲጂታል ኢኮኖሚ እና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ባለፉት 7 ዓመታት ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህን ለማስቀጠልም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሚል እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

እራሱን ችሎ የሥራ ዕድል እና ሀብት መፍጠር የሚያስችለውንና ሌሎች ዘርፎችን የሚያነቃቃው የዲጂታል አሰራርን በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ተቋማትም ሊተገብሩት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ኢቢሲም የዚህ ጉዞ አካል በመሆን በእራሱ አቅም ያበለፀገውን መተግበሪያ ለማስመረቅ በመብቃቱ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

በአፎምያ ክበበው

#EBC #ebcdotstream #Digital_EBC #DigitalEthiopia #EBCApp