የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቀን እና ሌሊት ባልተቋረጠ ቁርጠኝነት እየተገነባ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሠረተ ልማት ፕሮጀክት የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን መጎብኘታቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።
አውሮፕላን ማሪፊያው ሲጠናቀቅ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ለመቀበል እና ኢትዮጵያን ከዓለም ቀዳሚ የአቪዬሽን ማዕከላት ተርታ ለማሰለፍ ቀን እና ሌሊት ባልተቋረጠ ቁርጠኝነት እየተገነባ ይገኛል ነው ያሉት።